česky  english 

Advanced search
na_celou_sirku
Photo: (@MZV)
Article notification Print Decrease font size Increase font size

የቫትስላፍ ሃቨልን 80ኛ አመታት የልደት በአል አስመልክቶ ለተዘጋጀው ዓውደ-ርእይ የግብዣ ጥሪ::

እ.አ.አ ጥቅምት 2016 በቼክ ሪፐብሊክ በሃያኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻዎቹ አመታት በፖለቲካው ጉልህ ሚና የነበራቸውን የቀድሞው ፕሬዚደንት ቫትስላፍ ሃቨል 80ኛ አመት የልደት በአል የምንዘክርበት ወቅት ነው:: ይህንን ውድ ጊዜ ለማክበር በአዲስ አበባ የሚገኘው የቼክ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ባዘጋጀው “ቫትስላፍ ሃቨል: ፖለቲካዊ ህሊና እና ሃላፊነት” የተሰኘው የፎቶ ዓውደርእይ ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ይጋብዛል:: ዝግጅቱ እ.አ.አ ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 16/ 2016 በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ የሚካሄድ ይሆናል::

ይህ ዓውደርእይ የተዘጋጀው ፕራግ ውስጥ ከሚገኘው የቫትስላፍ ሃቨል ቤተ መጻሕፍት ጋር በመተባበር ሲሆን የሶስት ፎቶ አንሺዎችን (ኢቫን ፓጄር፣አልድሪች ስካቻ እና ኦንድሬጅ ነሜክ) ስራ በውስጡ የያዘ ነው:: እኚህም የቫትስላፍ ሃቨል ፎቶዎች በሃያኛው ክፍለ ዘመን በነበረው የህይወት ጉዞ የሚዳስሱ ሲሆኑ እ.አ.አ ከ1968 የፕራግ ጸደይ አንስቶ በ1989 የነበረውን የቬልቬት ሪቮሉሽን እና በቼኮዝሎቫኪያ በኋላም በቼክ ሪፐብሊክ የነበሩትን ሶስት ፕሬዚደንታዊ ዘመናት አካቷል::

የቫትስላፍ ሃቨልን 80ኛ አመት የልደት በአልን አስመልክቶ ከተዘጋጁት ሌሎች ፕሮግራሞች መካከል በቀድሞው ፕሬዚደንት ወንድም አቶ ኢቫን  ሃቨል የሚቀርበው ህዝባዊ ንግግር እ.አ.አ በጥቅምት 27, 2016 ከጠዋቱ 4 ሰዓት በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ የስእል ማሳያ አዳራሽ የሚቀርብ ይሆናል:: በዚያኑ እለት ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ “ዜጋ ሃቨል” የተሰኘው ጥናታዊ ፊልም በኤ.ኢ.ዔፍ ሲኒማ አዳራሽ ውስጥ በአውሮፓ የፊልም ፌስቲቫል አቅራቢነት የሚታይ ይሆናል::

የመጀመሪያው እና ዋነኛው ደራሲ፣ገጣሚ እና ፈላስፋው ቫትስላፍ ሃቨል ፖለቲካዊ ሥራውን የጀመረው የተቃዋሚዎች መሪ በመሆን ሲሆን በኋላም የመጨረሻው የቼኮዝሎቫኪያ ፕሬዚዳንት እና የመጀመሪያው የቼክ ሪፑብሊክ ፕሬዚዳንት ለመሆን በቅቷል:: የኔልሰን ማንዴላ፣ የቢል ክሊንተን፣ የኮፊ አናን፣የማዴሊን አልብራይት፣ የዳላይ ላማ፣የአንግ ሳን ሱ ኪይ እና ሌሎች በስልጣን ሆነ በተቃውሞ ውስጥ ከነበሩ በርካታ የዓለም ፖለቲካዊ እና መንፈሳዊ መሪዎች ጋር ጥብቅ የግል ወዳጅነት ነበረው:: ቫትስላፍ ሃቨል ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ መንግስታዊ ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን እንደ የፈረንሳዩ ግራንድ ክሮስ ለጅን ዲ ሆነር እና የዩናይትድ ስቴትስ ሀገራዊ የነፃነት ሜዳሊያ ይካተትበታል:: ይሁንና ለኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ሲመረጥ ሁል ጊዜ ሃሳቡን በመቃወም ለሌሎች እጩዎች የምርጫ ዘመቻ ያካሂድ ነበር::  ቫትስላፍ ሃቨል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለተገለሉ፣አቅም የሌላቸው እና የተጨቆኑ ሰዎችን የመጠበቅ ጠንካራ አቋም ነበረው:: የሃቨል ፖለቲካ ዋንኛ መርሆች ሕሊና እና ኃላፊነት ነበሩ፤ እነዚህም እሴቶች በዛሬው ዓለም በብዛት የተጓደሉ ናቸው:: ሃቨል በሕይወት ዘመኑ የጻፋቸው ብዙ ቃላቶች ተረቦች፣ ትኩረት የሚስቡ እና በእርግጥም ዘመን የማይሽራቸው ነበሩ::